Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከተሞች ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ማንሳትም ሆነ ማሻሻል እንደሚችሉ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ከዚህ በፊት ተጥሎ የነበረውን ሰዓት እላፊ ገደብ ወቅታዊ ሁኔታን ግምት ውስጥ በማስገባት ማንሳትም ሆነ ማሻሻል እንደሚችሉ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ወሰነ።
 
የአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ከአሁን ቀደም የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ በማሳለፉ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡
 
ይሁን እንጂ አሁን ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ አስተዳደር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ውይይት አድርጎ ውሰኔ አሳልፏል።
 
በዚህም በክልሉ የሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የሰዓት እላፊ ገደቡ ቢነሳ ምንም አይነት ስጋት የለብኝም ብለው ካመኑ ከካቢኔያቸው ጋር በመምከር እየገመገሙ ሰዓት እላፊውን ማንሳትም ሆነ ማሻሻል እንደሚችሉ ነው የክልሉ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔ ያሳለፈው።
 
በውይይቱም ከዚህ በፊት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ በክልሉ የሚገኙ ከተማ አስተዳደሮች ሙሉ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በመውሰድ፤ ሰዓት እላፊውን ማንሳትም ሆነ ማሻሻል እንደሚችሉ መወሰኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.