Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል የተከሰተውን የድርቁ ሁኔታ ለመቋቋም እየተሰጠ ያለውን ምላሽ ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የተቋቋመው የድርቅ ምላሽ ኮሚቴ የተከሰተውን የድርቅ ችግር ለመቋቋም እየተሰጠ ያለውን ምላሽና ያለበትን ደረጃ ገመገመ፡፡

ግምገማውን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የሚመራው አብይ ኮሚቴ የድርቁን ምላሽ የአመራር ሂደት በቀጥታ የሚመራ የጋራ ኮሚቴ አዋቅሯል።

በክልል ደረጃ የድርቁን ምላሽ የሚመራው አብይ ኮሚቴ ፥ የፕሬዚደንት ጽ/ቤት፣ የሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት፣ የአደጋ ስጋት አመራር ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮ እና የኮሙኒኬሽን ቢሮ ይገኙበታል፡፡

በዞንና በወረዳ ደረጃም አስተዳዳሪ ጽ/ቤቶች፣ የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ መመሪያ ጽ/ቤት፣ የዞኖች ጸጥታና ደህንነት መመሪያ ጽ/ቤት እና የአደጋ ስጋት አመራር እና ሌሎች የጽህፈት ቤት ተወካዮች እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

በተጨማሪም ለተከሰተው ድርቅ የሚደረገውን እርዳታ የሚከታተል ኮሚቴ ተቋቁሞ ኮሚቴው ለድርቁ አደጋ ለመከላከል የተመደበውን ባጀት ያለአግባብ እንዳይጠቀም እንዲሁም እርዳታው ለታለመለት ዓላማ መዋሉንና ተጠያቂነትን እንደሚያረጋግጡ ተገልጿል።

ኮሚቴዎቹም ከምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ፣ የፕላን ጽ / ቤት ክትትል ኮሚቴ፣ የክልሉ ዋና ኦዲተር ፣ ፀረ-ሙስና ኮሚሽንና የክልሉ ፍትህ ቢሮ መ/ቤቶች እንደሚዋቀሩም ተገልጿል፡፡

የሶማሌ ክልል ካቢኔ አባላትና የመንግሥት ተሿሚዎች ከወርሃዊ ደሞዛቸው ለድርቁ ምላሽ የሚውል 20 ሚሊየን ብር እንደሚለግሱ መገለጹን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.