የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የገና እና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ከወጣቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው – ፖሊስ

By Meseret Awoke

January 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና እና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ፖሊስ ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ፥ ፖሊስ ከከተማዋ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት የመዲናዋን ሰላም እያሰጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ለገና እና ለጥምቀት በዓላት ሰላማዊነት ደግሞ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው የጠቆሙት ።

ከተለያዩ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዳያስፖራዎችና የኢትዮጵያ ወዳጆችም በመዲናዋ የትኛውም አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው ፖሊስ የተጠናከረ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ገልጸዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች በሃላፊነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!