ቴክ

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለ5 ከተሞችና ለ6 የፌደራል ተቋማት ፖርታሎችን አልምቶ አስረከበ

By Alemayehu Geremew

January 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለጅግጅጋ፣ ሀረር፣ ጋምቤላ፣ ጅማ ፣ ሆሳዕና ከተሞች እና ለስድስት የፌደራል ተቋማት ፖርታሎችን አልምቶ አስረከቧል፡፡

ፖርታል የለማላቸው የፌደራል ተቋማት፥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ÷የመንግስት አገልግሎቶች በሂደት ወደ ዲጂታል የአስራር ዘዴ የሚቀየሩበትን ስልት በመንድፍ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራን ነው ብለዋል።

የከተሞችና ተቋማት ፖርታሎች የዜጎች ታማኝና የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ሊሆኑ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ ባለሙያዎች ፖርታሎቻቸው የዳበረና አዳዲስ መረጃ እንዲይዙ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ፖርታሎቹ የከተሞቹንና የተቋማቱን ልዩ አወቃቀር፣ አገልግሎቶቻቸውን እና የቱሪስት መስህቦች መረጃዎችን አጠቃለው የያዙ መናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።