የሀገር ውስጥ ዜና

የገና በአልን በላሊበላ ለማክበር እንግዶች ከተማዋ እየገቡ ነው

By Mekoya Hailemariam

January 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ)  የገና በአልን በላሊበላ ለማክበር እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው።

በዓሉን ለማክበር እየገቡ ያሉት እንግዶች በሃገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ናቸው።

በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ውስጥ ቆይታ ነፃ የወጣችው የላሊበላ ከተማ በየዓመቱ የገና በዓል በድምቀት ይከበርባታል።

በወረራው የተጎዳውን የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያነቃቃል ተብሎ በታመነበት በዘንድሮው የገና በዓልም የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

 

በለይኩን ዓለም