Fana: At a Speed of Life!

ፍቅርና የአንድነት እሴቶቻችንን በማጠናከር በዓሉን ማክበር እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያውያን እሴቶች የሆኑትን ፍቅርንና አንድነትን በማጠናከር የልደት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የገና በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት ገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በድል ማግስት ለሚከበረው የብርሃነ ልደቱ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በመልዕክቱ በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተሞከረውን አገር የማፍረስ ሴራ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት መክተን ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና ቀጥላለች ብሏል።

በዓሉ ለኢትዮጵያውያን ድርብ ደስታ የፈጠረ መሆኑን ጠቁሞ÷ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ከእኛ ጋር ለማክበር በመምጣታቸው የኢትዮጵያን ጠላቶች አንገት ማስደፋቱን ገልጿል።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የኢትዮጵያውያን እሴቶች የሆኑትን ፍቅርንና አንድነታችን በማጎልበት፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋ ባህላችንን የሚሸረሽር መለያየትና ጥላቻን በመቅበር፣ ከመራራቅ ይልቅ መቀራረብንና መደመርን በማጉላት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ነው ምክር ቤቱ የገለጸው፡፡

የተቸገሩትን በመታደግ፣ ለጋራ ዓላማ በመትጋት በንጹሃን ላይ ግፍ የሚፈጽሙትን ዕብሪተኞች ህልምና ትልማቸውን በማክሸፍ ፣ አገራችን የሰነቀችውን ተስፋ ዕውን በማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ወርቃማ ታሪክ ለመጻፍ በመትጋት ጭምር ሊሆን ይገባልም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞና ትንሳዔ በሚያፋጥኑ ጥረቶች ላይ በሚደረገው ርብርብ የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቤት የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጎላ ድርሻ እንዳለውም አመላክቷል።

ምክር ቤቱ የተጣሉበትን አገራዊ ኃላፊነቶች እንዲወጣ ሁሉም በየተሠማራበት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳበትም አሳስቧል።

በዓሉ ለኢትዮጵያውያን የብልጽግና፣ የደስታ፣ የሠላምና የአንድነት እንዲሆን መመኘቱን የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.