Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን ባስጠበቀ መልኩ ከሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲ እንዲኖራት እየሰራች ነው -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2022 ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን ባስጠበቀ መልኩ ከሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲ እንዲኖራት እየሰራች መሆንዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

በፈረንጆቹ 2021 ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበረና ይህንንም ለመቋቋም በተደረገው ጥረት ውጤታማ ስራ መሰራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀይሎች በደረሰባት ጫና የገጠማትን ችግር ለመቋቋም ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ ሀገራት እንዳሉ የገለጹት አምባሳደሩ፣ ጀርባ የሰጡ ሀገራት እንደነበሩም ጠቁመዋል።

በፈረንጆች 2022 ኢትዮጵያ የተጠናከረ ዲፕሎማሲ ከተለያየ ሀገራት ጋር እንዲኖራት ጠንክራ ትሰራለች ብለዋል ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።

በቅርቡ የአስር ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል።

በአዳነች አበበ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.