የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን ባስጠበቀ መልኩ ከሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲ እንዲኖራት እየሰራች ነው -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

By Feven Bishaw

January 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2022 ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና ነጻነቷን ባስጠበቀ መልኩ ከሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲ እንዲኖራት እየሰራች መሆንዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

በፈረንጆቹ 2021 ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበረና ይህንንም ለመቋቋም በተደረገው ጥረት ውጤታማ ስራ መሰራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።