Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጀግንነት አሸባሪውን ቡድን የመከተውን የሀደሌኤላ ወረዳ እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጀግንነት አሸባሪውን ቡድን ወደ መከተው የሀደሌኤላ ወረዳ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
የሀደሌኤላ ወረዳ አሸባሪው የህውሃት ቡድን ከህዳር 19 ጀምሮ ከደብረሲና ሸሽቶ አዋሽን ለማቋረጥ ሲሞክር የአካባቢው ሚሊሻና አርብቶ አደር በጋራ በመሆን ከ600 በላይ የአሸባሪውን ቡድን መደምሰስ ችለዋል።
ቡድኑ በኋላም ከባድ መሰሪያ በመጠቀም አካባቢውን በማጥቃት የተለያየ ውድመት አድርሷል።
በከተማዋ በቆየበት ጊዜ ከግለሰብ ጀምሮ የመንግስት ንብረቶችን ማውደሙ ተገልጿል፡፡
የወረዳው አስተዳደር የአሸባሪውን ቡድን አላማና ባህሪ አስቀድሞ ስላወቀ ከሚሊሻው ጋር በመሆን ህጻናትንና ሴቶችን አስቀድሞ ከአካባቢው ማሸሽ በመቻሉ በህጻናትና ሴቶች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል።
አሁን ወረዳው ከክልልና ከፌደራል ባገኘው ድጋፍ ወደቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴው ተመልሷል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፥ አንድም የመከላከያና ልዩ ሃይል ሳይኖር የሀደሌኤላ ወረዳ ሚሊሻና አርብቶ አደር ለአሸባሪው ቡድን የአፍርን ልክ አሳይተውታል ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን በወረዳው እሬሳና ቁስለኛ ማንሳት ሳይችል እንደሸሸም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ለኢትዮጵያ ክብርና ሉአላዊነት መከበር የሚከፈለው መስዋዕትነት ሁሉ ይከፈላልም ብለዋል።
የ27ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ጥላሁን፥ የአፋር ህዝብ ሁሌም ሀገሩ ሲነካበት ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ ብሎ መነሳት ልማዱ ነው ፣ አሸባሪው ቡድን ወደ ክልሉ ሲገባ መቀበሪያውን አዘጋጅቶ ነው ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ ለመከላከያው ደጀን በመሆን በሁሉም ግንባር አጋርነቱን አሳይቷልም ነው ያሉት ።
ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ሲጠብቁ የነበሩ ጠላቶቻችንን በውትድርናም በዲፕሎማሲም በማሸነፍ አሳፍረናቸዋልም ሲሉ ገልጸዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ፥ ጠላት ማንነታችንን ለማፍረስ ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ መንገድ ሲሰራ ቢቆይም ሁሉም ከመከላከያ ጎን በመቆም ጠላትን ወደመጣበት መቅበር ተችሏል ብለዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚሆን 500 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፥ ድጋፉ በቀጣይም የሚቀጥል እንደሆነ አክለው ገልጸዋል።
በዘላቂነት ተጎጂዎችን ለመደገፍም የአፋር ጀግኖች ፈንድ እንደሚቋቋም ገልጸዋል።
በዘመን በየነ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.