Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ደገም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ ።
 
በዛሬዉ እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ ነው አደጋው የደረሠው ።
 
አደጋው የደረሰው መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ የእርዳታ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከኩዩ ወረዳ ወደ ፊቼ ከተማ 13 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ ከነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
 
በዛሬው እለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ በተከሰተው አደጋም የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ደህንነት ዲቪዥን ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታደሰ ሌጂሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
 
በአደጋው የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪውን ጨምሮ በሚኒባሱ ተሳፍረው በነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷አሁን ላይም በፊቼ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
 
አደጋውን በማድረስ የተጠረጠረው የጭነት መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ነው የገለጹት፡፡
 
በሳምራዊት የስጋት
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.