Fana: At a Speed of Life!

የገና በዓልን አስመልክቶ ለመቄዶኒያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ከ27 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽንና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የገናን በአል አስመልክቶ ለመቄዶኒያ የአረጋዉያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ከ27 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በዛሬዉ እለት የ27 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገልፀዋል፡፡
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፥ በትብብር እና በአንድነት መስራት ከተቻለ የማናሸንፈዉ ችግር የለም ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑም ሆነ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሌም እገዛቸውን በጠየቅን ጊዜ ፈጥነዉ ምላሽ የሚሰጡን በመሆናቸዉ ለሌሎችም አርአያ የሚሆኑ ተቋማት ናቸው ሲሉ የማህበሩ መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ ገልጸዋል፡፡
በማህበሩ ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸዉ ድጋፍና ለተሰጣቸዉ ፍቅር ምስጋና አቅርበዉ በውስጥም በውጭም ላሉ ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ድጋፉ አልባሳት፣ ምግብ ነክ፣ የማብሰያ እቃዎችና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.