Fana: At a Speed of Life!

በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ላይ ያተኮረ ውይይት በላሊበላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ፣ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ስላሴና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች እየቀረቡ ሲሆን ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በውይይቱ ዶክተር ይልቃል ከፋለ፥ በአሉን ከወራት በፊት በዚህ መልክ እናከብራለን ብለን አላሰብንም ነበር ሆኖም አሁን ሰላም ሆኖ ለማክበር በቅተናል ብለዋል።

ላሊበላ የቱሪስት ከተማ በመሆኗ ወደ ቀደመ መልኳ እንድትመለስ ለማድረግ ሊሰራ ይገባል ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በዚህም የዘንድሮው የገና በዓል በታላቅ ድምቀት እንዲከበር ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በለይኩን አለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.