Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮ ገና በብዙ ድሎችን ታጅቦ የሚከበር በአል ነው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የዘንድሮ ገና በብዙ ድሎችን ታጅቦ፤ በኢትዮጵያዊነትና በህብረብሔራዊ አንድነት አምሮና ተንቆጥቁጦ የሚከበር በአል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስትላልፈዋል።

የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

 

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ !!

ይህ በአል በተለይም ዘንድሮ በብዙ ድሎቻችን ታጅቦ፤ በኢትዮጵያዊነትና በህብረብሔራዊ አንድነት አምሮና ተንቆጥቁጦ የሚከበር በአል ነው፡፡

ለእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ክፉዋን የሚመኙትን አሳፍሮ ለህመምዋ ሳይሆን ለፈውሷ የሚተጉን ልጆቿ ክንድ አበርትታ የተከፈተባትን ወረራና ጦርነት በመመከትና ይበተናሉ ፣ ይፈርሳሉ ሲሉን በአንድነትና በፅናት በመቆም ወራሪዎችን እንድናሳፍር የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !!

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያችን ድምፅ በመሆን በአለም አደባባዮች በከፍተኛ ወኔ የሞገቱ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመሪያችንን ጥሪ ሰምተው ተሰብስበው ወደ ሃገር በመግባት ለሃገራችን ይህ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ወቅት መሆኑን ያሳዩበት ነው ፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ መሆኑን ዳግም ያረጋገጥንበትና መጪው ጊዜ በአንድነት የሚስጥር ቁልፍ በርካታ የስኬት በሮችን እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንከፍትበት ፤ በጎጇችን ስር ተመካክረንና ተወያይተን የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ይሆናል፡፡

በአሉን ስናከብር የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ፤ የታረዙ ፤ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችንን በመድረስና መልሶ በማቋቋም ፣ የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ ፣ ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊታችንን በማበረታታት ፣ ኢትዮጵያዊ የመተጋገዝ ባህላችንን በማስቀጠል በመተሳሰብና በአብሮነት ሊሆን ይገባዋል፡፡

ትብብራችን አሸናፊ ነው! የድላችን ሚስጥር አብሮነታችን ነው!

መልካም በአል ይሁንልን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.