ቢዝነስ

የጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

January 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በታህሳስ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወርም ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በጥር ወር 2014 ዓ.ም የአውርፕላን ነዳጅን ጨምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ያለምንም ለውጥ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል፡፡