Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ  ትልቅ የተባለውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛ ነው የተባለውን የጥናት ውጤት ይፋ  አደረገች።

በዚህም አዛውንቶችና  እና ህመምተኞች ለኮሮና ቫይረስ  ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን  ተገልጿል፡፡

በጥናቱ ከ70 ሺህ በላይ የበሽታው ዝርዝር ጉዳዮች መገለጻቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የቻይና የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ይፋ እንዳደረገው ÷ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆው ይህ ወረርሽን በበሽተኞች እና አዛውንቶች ተጋላጭ መሆናቸው ጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪም የሕክምና ባለሞያዎችና  ሠራተኞች ከፍተኛ ተጋላጭነን እንደሆኑ  በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

በአብነትም የ51 ዓመቱ የውሃን ሆስፒታል ዳይሬክተር የሆኑት ሊዙ ዙሚንግ  በቫይረሱ መሞታቸው ቀርቧል፡፡

የሁቤይ  ግዛት በሀገሪቱ በቫይረሱ እጅግ የተጎዳች  መሆኗም ነው የተነገረው፡፡

በአካባቢው ያለው የሞት መጠን 2 ነጥብ 9 በመቶ ሲሆን በሌላው የሀገሪቱ አካባቢ 0 ነጥብ 4በመቶ ብቻ መሆኑም ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በቻይና የኮቪ -19 ቫይረስ አጠቃላይ የሞት መጠን በ 2 ነጥብ 3 በመቶ መቀነሱ ነው ጥናቱ ያመለከተው፡፡

ባለስልጣናቱ አያይዘውም ከ 12 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውንም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.