የሀገር ውስጥ ዜና

በላሊበላ መስቀል ክብራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አሸባሪው ህወሓት በግፍ የገደላቸውን ንፁሃን አስከሬን መቅበሩ ተገለጸ

By Meseret Awoke

January 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በላሊበላ ከተማ በሚገኘዉ መስቀል ክብራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ አሸባሪው ህወሓት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊቶችን ፈፅሟል።

አሸባሪ ቡድኑ በትምህር ቤቱ ከፈጸማቸው አስነዋሪ ድርጊቶች መካከል በግፍ የገደሏቸዉን ንፁሃን አስከሬን በቅጥር ግቢ ውስጥ በጅምላ መቅበሩ አንዱ ነው።

በተጨማሪም በመንግስትና በበጎ አድራጊዎች ከ800 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተደራጀውን ቤተመፃህፍት ሙሉ በሙሉ በማዉደም የጭካኔ በትሩን እንዳሳረፈበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ረዳ ሲሳይ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!