Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሰራዊት ሲጠቀምባቸው በነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገለጸ፡፡
 
የመከላከያ ሰራዊት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ እንዳስታወቀው÷ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
 
በዚህ መሰረትም በምልክቶቹ ውስጥ ጋሻና አንበሳን ጥቅም ላይ ማዋሉን ነው የገለጸው።
 
ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ምልክቶች ሀገራዊና ታሪካዊ ይዘታቸው የጎላ እንዳልነበርም ጠቁሟል፡፡
 
ሰራዊቱ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ካስፈለገ፤ አርማውም ማዕረጉም ስርዓት ሲለወጥ መቀየር የሌለባቸው ሆነው እንዲቀመጡ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማእከል ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል መስፍን ለገሰ÷ አዲስ የተሻሻሉት ወታደራዊ የማዕረግ ምልክቶችም ሀገራዊ እና ታሪካዊ ይዘቶችን ከግምት ያስገቡ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
 
የሠራዊቱ የማዕረግ ምልክት በዋናነት አንበሳውን ሰራዊታችንን እና ህዝባችንን በሚገልፀው የአንበሳ ምልክትና የአገር ሉዓላዊነትና ክብር የማስጠበቃችን ምልክት የሆነውን ጋሻ እንዲያካትት ተደርጎ ተመዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡
 
በሀብታሙ ተክለስላሴ

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.