Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጠቁ የራሶ ወረዳ ተጎጂዎች አስቸኳይ እርዳታ እየቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግስት በድርቁ ለተጠቁ የራሶ ወረዳ ተጎጂዎች አስቸኳይ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ገለጸ፡፡
 
በድርቁ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አከባቢዎች አንዱ በሆነው በአፍ-ዴር ዞን ራሶ ወረዳ ተጎጂ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።
 
በዚህ መሰረትም በአሁኑ ወቅት በራሶ ወረዳ በሚገኙ 12 አከባቢዎች የሚኖሩ ተጎጂ ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ማዳረስ ስራ በአግባቡ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በዚህ ወር በወረዳው ሥር የሚገኙ ተጨማሪ 6 አከባቢዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ስራዎችን ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁንም ነው አስተዳደሩ የገለጸው።
 
የድርቁ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ የተንሰራፋውን ህዝብ ፍልሰት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.