Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያዊነትን ሊያጸና የሚችል መድረክ መሆን ይኖርበታል – አቶ ግርማ ሰይፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የምክክር መድረኩ ኢትዮጵያዊነትን ሊያጸና የሚችል እንጂ የምንነታረክበት መድረክ መሆን የለበትም ሲሉ ፖለቲከኛው አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ ።
የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ግርማ ሰይፉ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፥ አገራዊ የምክክር መድረኩ በዋነኝነት የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ሊያጸና የሚችል እንዲሁም መግባባት ላይ እንድንደርስ የሚያስፈልግ ሥራ እንድንሰራ የሚያስፈልገበት ነው ብለዋል ።
ከዚህ ውጪ ተራ ጭቅጭቆችን ይዘን የምንነታረክበት መድረክ መሆን የለበትምም ብለዋል።
አንድ ሺህ አጀንዳዎችን የምናይበትም አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ ውስጥ ሳንመካከርባቸው ያሳደርናቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ ያሉት አቶ ግርማ ፥ የማያጣሉንን ጉዳዮች ቁጭ ብለን ብናወራቸው ልንፈታቸው የምንችለው ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ነው ሲሉም አንስተዋል።
ምክክሩ እነዚህን ጉዳዮች በመፍታት ወደ አገር ግንባታው ለመሄድ ዕድል የሚፈጥር ተግባር በመሆኑ በበጎ ጎን እንደሚያዩትም ገልጸዋል ።
የተወሰኑና አገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች የሚታዩበት ብቻ ይሆናል ብለን እናምናለን ነው ያሉት ።በዚህም ምክክሩ ተራ ጭቅጭቅ ሳይሆን አገርን ሊያጸና የሚችል መሆን እንዳለበት ገልጸዋል ።
በምክክር ሂደቱ ሁሉም ሰው ድርሻውን አለመቀላቀል እንደሚጠበቅበትና የሚመለከተውን ብቻ ማድረግ እንዳለበት ጠቅሰው ፥ ይሄንን በግልጽና በተሟላ ሁኔታ ለይቶ ማስኬድ ከሁሉም አካል እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል ።
አቶ ግርማ አያይዘውም እንደመደበኛ ስህተት ከሚታዩት ስህተቶች ውስጥ አገር የፖለቲከኞች ብቻ የሚመስላቸው አሉ ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ፖለቲከኛው ከተስማማ አገር የሚስማማ የሚስላቸውም አሉ ። በአንጻሩ አንዳንዱ ደግሞ የየሰፈሩና የየቀበሌው ችግር የአገር ችግር የሚመስለው አለ ።ብዙ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ችግሮች አሉ ።እነዚህን ችግሮች በምክክር መፍታት ነው የሚያስፈልገው ።ከዚህ ውጪ አገርን የፖለቲከኞች ብቻ አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
ከአሁን ቀደም ከስብሰባ በዘለለ “አገራዊ ምክክር” በሚል ደረጃ ውይይቶች እንዳልነበሩና ይህም በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ገልጸዋል ።
ይህ አገራዊ ምክክር ባይሳካስ ተብሎ ለሚነሳ ሃሳብም ሌላ አገራዊ ምክክር እንሞክራለን እንጂ አገር አይፈርስም ማለራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.