Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች የደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎችን ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሾቤ አካባቢ ተገኝተው የደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎችን ሰብስበዋል፡፡
የዳያስፖራው ማህበረሰብ በዚህ መልኩ የአርሶ አደሩን ሰብል መሰብሰብ ታላቅ ሀገራዊ ኩራት መሆኑን የክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም የአረጋውያንና የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ፣ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ዳያስፖራው እዚህ ተገኝቶ ሰብል መሰብሰቡ ኢትዮጵያውያን ያለንን የጠነከረ ህብረት ለመላው ዓለም ለማሳየት ይጠቅማል ያሉት ደግሞ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፋኖሴ ደቻሳ ናቸው፡፡
የዲያስፖራው አባላት በበኩላቸው÷ በህብረት ሆነው ሰብል መሰብሰባቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው÷ ወደፊትም በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎች በመጓዝ የተጎዱ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ከክፍለ ከተማው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.