Fana: At a Speed of Life!

የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሴራ” ነገ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሴራ” ነገ በሲምፖዚየም እንደሚከበር የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አስታወቁ፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ ጥር 1 ቀን 2014 በዞን ደረጃ የሚከበረውን የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሴራ” አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በወረዳ ደረጀ በየዓመቱ በዞን ደረጃ ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚከበረው የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሴራ” ዘንድሮ በሲምፖዚየም እንዲከበር ተወስኖ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
እንደ ሀገር በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የተጋረጠብን ጦርነት ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ የ “ሴራ” በዓልን በድምቀት ማክበር ባይቻልም “ሴራ” የብሔረሰቡ ወርቃማ እሴትና አንዱ የልማት ግምባርም በመሆኑ በሲምፖዚየም ታስቦ እንደሚውል ነው አስተዳዳሪው ያስታወቁት።
የዘንድሮው “የሴራ” በዓል በአለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት መከበሩ ከሌሎቹ ጊዜያት ለየት እንደሚያደርገው መግለጻቸውንም ከሃላባ ሚዲያ ኔትወርክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በኢትዮጵያና በተለያዩ የዐሰለም ሀገራት ለሚገኙ ለመላው የብሔረሰቡ ተወላጆች እና ወዳጆች ዋና አስተዳዳሪው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, beard and standing
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.