የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት የተወሰኑ እስረኞችን ክስ በማቋረጥ ከእስር መፍታቱ ለአገራዊ ምክክሩ አካታችነት ጉልህ ፋይዳ አለው- ፍትህ ሚኒስቴር

By Feven Bishaw

January 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የተወሰኑ እስረኞችን ክስ በማቋረጥ ከእስር መፍታቱ የአገራዊ ምክክሩን አካታችነት፣ ሰብአዊነትና ርህራሄን ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

ከፖለቲካ ልሂቃን አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እየተንጸባረቁ ያሉ ያለመግባባት ችግሮችን በአገራዊ ምክክር ከስር መሰረቱ ለመመፍታት በመደበኛ ፍትህ ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል።