Fana: At a Speed of Life!

ህብረቱ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉ በአማራ ክልል ሸዋ ሮቢትና ደብረሲና ከተሞች እንዲሁም በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ወረዳ ለሚገኙ ወገኖች ነው የተሰጠው።
 
ጦርነቱ በርካታ ዜጎችን ለችግር መዳረጉን የገለጹት የህብረቱ ሰብሳቢ ዶክተር ንጉሱ ለገሰ÷ ለዚህም ጠንካራ ትብብርና መደጋገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
 
በጦርነቱ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለማገዝ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 550 ካርቶን የምግብ ዘይት፣ 11 ቦንዳ ብርድ ልብስ፣ አንድ ሺህ 116 ካርቶን ፓስታ፣ 260 ኩንታል የዳቦ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን ነው የተናገሩት።
 
ለአፋር ክልል ሰሙሮቢ ወረዳ 440 ካርቶን ዘይት፣ 176 ኩንታል የዳቦ ዱቄት፣ 446 ካርቶን ፓስታ፣ 50 ፍራሽ፣ 3 ቦንዳ ብርድ ልብስና ሌሎች ድጋፎች የተሰጡ ሲሆን÷ ቀሪው ለአማራ ክልል ሽሜ ሽዋ ዞን ሽዋ ሮቢትና ደብረሲና ከተማ ተፈናቃዮች እንዲደርስ የተደረገ ነው ብለዋል።
 
በቀጣይም በየአካባቢው በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በመለየት በመልሶ ግንባታ ለመሳተፍ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች የሥነ ልቡና ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ከአካባቢው አስተዳደሮች ጋር ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በባው መለሰ፥ ህብረቱ ችግር በደረሰባቸው አካባቢዎች ተዘዋውሮ ጉዳቱን ለመለየት ያደረገው ጥረት ተገቢ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአፋር ክልል የሰሙሮቢ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፀጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሁመድ አደም በበኩላቸው÷ ለተደረገው የምግብና የሌሎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማመስገናቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.