Fana: At a Speed of Life!

ካዛኪስታን ከሩሲያ በጠየቀችው ወታደራዊ ድጋፍ ላይ አሜሪካ የሰጠችው አስተያየት በሞስኮ ክፉኛ ተተቸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ካዛኪስታን በሀገሯ ለገጠማት የፀጥታ ስጋት ምላሽ ለመስጠትለሩሰያ ባቀረበችው የወታደራዊ ድጋፍ ጥያቄ ላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የሰጡትን አስተያየት ሞስኮ ክፉኛ ተቸች።

ካዛኪስታን ሩሲያ ለምትገኝበት የዩሮዢያ ወታደራዊ ጥምረት የድጋፍ ጥያቄ አቅርባለች።

በዚህ ጥያቄ መሰረት ሞስኮ ወደ ካዛኪስታን ወታደር መላኳ ህጋዊ አካሄዱን የተከተለ እንደሆነ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ በጻፋት መልእክት ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባይዋ ይህንን ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢሊንከን “የሩሲያ ሃይሎች አንዴ ወደሀገሪቱ ከገቡ ለቀው እንዲወጡ ማድረግ ከባድ ነው” በማለት አስተያየት ከሰጡ በኋላ ነው፡፡

ማሪያ ዛካሮቫ የብሊንከንን አስተያየት አግባብነት የሌለው ቀልድ ነው ብለውታል ፡፡

ይልቁንም እውነታው አሜሪካውያን አንዴ ወደቤታቸን ከገቡ በህይወት መቆየት፣ ሳይዘረፉ ወይ ሳይደፈሩ መኖር አዳጋች መሆኑ ነው ብለዋል። ያለፉት 300 አመታት ታሪክም ያስተማረን ይህን ነው በማለት የአሜሪካ መንግስት ሳይጋበዝ ጣልቃ በመግባት በቬትናም፣ ኮሪያ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ ዩጎዝላቪያ እና ሌሎች ሀገሮች ያስከተላቸውን ቀውሶች ዘርዝረዋል።

በካዛኪስታን የጋዝ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የተቀሰቀሰውን አመፅ ለመቆጣጠር የሀገሪቱ መንግስት ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ የሶቪየት ህብረት ሀገራትን በአባልነት ከያዘው የዩሮዢያ ወታደራዊ ጥምረት ወታደረዊ ድጋፍ ጥያቄ ማቅረቡን የአናዶሉ ኤጀንሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.