Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የምሳ ግብዣና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የምሳ ግብዣ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የምሳ ግብዣ እና የቁሳቁስ ድጋፉ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ዳያስፖራውን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላትን በማስተባበር የተደረገ ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሼቴ፥ ለመከላከያ የሚደረግ ድጋፍ ሀገርን ለማዳን፤ የቁርጥ ቀን ጀግኖችን አረዓያ ለመከተልና የሀገር ፍቅር ስሜትን ለመግለጽ የሚከናዋን መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው፥ የሠራዊቱ አባላት የህይወት መስዋዕትናትን የሚጠይቅ ውለታ ለሀገራቸውና ለህዝባችው በማዋላቸው ምስጋና ለማቅረብ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሃብታሙ ጥላሁን ሰራዊታችን የጀግንነቱ ሚስጢር ህዝብ ነዉ ማለታቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.