የሀገር ውስጥ ዜና

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የምሳ ግብዣና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

January 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለሚገኙ የሠራዊቱ አባላት የምሳ ግብዣ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የምሳ ግብዣ እና የቁሳቁስ ድጋፉ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ዳያስፖራውን ጨምሮ ሌሎች አጋር አካላትን በማስተባበር የተደረገ ነው፡፡