ለአገርና ለወገን አለኝታነታችንን የምናሳየው ተርፎን ሳይሆን ካለን ቀንሰን ነው -ዳያስፖራዎች
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”ለአገርና ለወገን አለኝታነታችንን የምናሳየው ተርፎን ከምንሰጠው ሳይሆን ካለን ቀንሰን በምናደርገው ድጋፍ ነው”ሲሉ ከጀርመን ፍራንክፈርት የመጡ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ገለጹ፡፡
አሸባሪው ህወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች በወረራ ይዟቸው በቆየባቸው አካባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ ባሻገር ህጻናትና አረጋዊያንን ጭምር አስገድዶ ደፍሯል፤ ከፍተኛ ቁሳዊ ውድመትም አድርሷል፡፡
በዚህ የሽብር ቡድን ሰለባ የሆኑ ዜጎችን መልሶ ማቋቋምና ወደቀደመ ኑሯቸው መመለስ ደግሞ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው ከጀርመን አገር የመጡ ዳያስፖራዎች ጠቁመዋል።
“ማንኛውም ዜጋ ለአገሩና ለወገኑ አለኝታ መሆኑን የሚያሳየው ከተረፈው ላይ ሳይሆን ካለው ላይ ቀንሶ በመስጠት ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
በውጭ የሚኖረው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አገሩን በማገዝ ወገናዊ አለኝታነቱን ማሳየት እንዳለበትም ነው ያነሱት፡፡
ዳያስፖራው በተለይም ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ላይ የወደሙ ተቋማት፣ ሆስፒታሎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት እንዲሁም ዜጎችን በማቋቋም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጉዳት የእያንዳንዱን ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ዜጎች እንድነታቸውን ጠብቀው በመደጋገፍ በጋራ ችግሩን ማለፍ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ አኳያ በችግር ወስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመደገፉን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ስራ ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!