Fana: At a Speed of Life!

100 ፊኛዎችን በ23 ሰከንድ በእግሩ ያፈነዳው አሜሪካዊ የአለም ክብረ ወሰን ሰበረ

አዲስ አበባ፣የካቲት10፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ነዋሪነቱ በኢዳሆ የሆነው አሜሪካዊ በ23 ነጥብ 69 ሰከንድ በእግሩ 100 ፊኛዎችን በማፈንዳት የአለም ክበረ ወሰን ሰብሯል፡፡

ዴቪድ ሩሽ የተባለው ግለሰቡ ሣይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ ና የሂሳብ (ስቲኢም)ትምህርቶችን  ለማሳደግ በሚል አላማ  ከ 100 በላይ ክብረወሰኖችን መስበሩ ነው የተገለጸው፡፡

ዴቪድ ይህ ሙከራው ለወጣቶች  የእድገት አስተሳሰብን፣ውድቀቶችን እና መሰናክሎችን ለማሸነፍ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማስተማር የሚረዳ  ነው ብሏል ፡፡

ግለሰቡ ክብረ ወሰኑን ለመስበር ሁለት ሙከራዎችን ብቻ እንዳደረገ ገልጾ÷ በመጀመሪያው ሙከራ በርካታ  የፊኛ ኳሶችን  ከመስመራቸው ተስፈንጥረው ሳያፈነዳ መቅረቱን ተናግሯል፡፡

በሁለተኛው ሙከራው ወቅት ሁሉንም የፊኛ ኳሶች   በ23 ነጥብ 69 ሰከንዶች አፈንድቶ መጨረሱን ተናግሯል፡፡

በዚህ ሙከራው አምልጣው የነበረውን አንዷ ፊኛ ጨምሮ ሁሉንም የፊኛ ኳሶች   በ23 ነጥብ 69 ሰከንዶች አፈንድቶ መጨረሱን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፡-https://www.upi.com/Odd_News

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.