ስፓርት

ዛሬ ምሽት ዋሊያዎቹ ከካሜሩን አቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

By Feven Bishaw

January 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን አቻው ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋል፡፡

በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ተጠባቂ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከካሜሩን አቻው ጋር ያደርጋል፡፡