የሀገር ውስጥ ዜና

በህገ-ወጥ መንገድ ከጅግጅጋ ወደ ሶማሌላንድ ሊወጣ የነበረ ነዳጅ ተያዘ

By Alemayehu Geremew

January 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሊወጣ የነበረ 2 ሺህ 820 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለት 2 ሺህ 820 ሊትር ነዳጅ በ141 ጀሪካን በአውቶብስ ተጭኖ በህገወጥ መንገድ ከጅግጅጋ ከተማ ሊወጣ ሲል ነው በሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የክትትል ባለሙያዎች የተያዘው፡፡

በሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርትና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዳይሬክተር መሀሙድ አሊ እንደተናገሩት ÷ በክልሉ የሚካሄደውን ህገ ወጥ የነዳጅ ፍሰት ለማስቆም ኅብረተሰቡ ከመንግሥትና ክትትል ባለሙያዎች ጋር ቆሞ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጅግጅጋ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እየታየ መምጣቱንና ህገ-ወጦች ነዳጁን ወደ ጎረቤት ሀገር ሶማሌላንድ ከተሞች ሲልኩ እንደነበር መረጃ ማግኘቱን ነው ያመለከተው፡፡