ስፓርት

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በጎንደር ተካሄደ

By Meseret Awoke

January 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሄደ።

ለስፖርት ክለቡ ሃብት ማሰባሰቢያ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫው የዘንድሮው መርሃ ግብር መነሻውን ማራኪ ፕላዛ ሆቴል አድርጎ መስቀል አደባባይ መጠናቀቂያውን አድርጓል፡፡

በጎዳና ላይ ሩጫው ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደተካፈሉበት የደጋፊ ማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ደመላሽ አበበ ገልፀዋል።

ጎንደር ከተማ ከምታከብረው ደማቁ የጥምቀት በዓል ሳምንት አካል እንደሆነ የተነገረለት ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ በወንዶቹ ሀብታሙ ብርሀኑ በሴቶች ደግሞ ሳምራዊት ይርጋ በአሸናፊነት እንዳጠናቀቁ ታውቋል።

በኤልያስ አንሙት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!