የሀገር ውስጥ ዜና

ለኢትዮጵያ ብሎም ለአዲስ አበባ በዚህ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን ማስተናገድ ትልቅ እድል ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Meseret Awoke

January 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአዲስ አበባ በዚህ ወቅት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ማስተናገድ ትልቅ እድል ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክትና በሰጡት የስራ መመሪያ እንደወትሮው ሁሉ ከሀገር ወዳዱና ጨዋዉ የከተማው ህዝብ ፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከፀጥታ አካሉ ጋር በጋራ በመሆን በተሟላ፣ ባማረና በተዋበ ሁኔታ ለማስተናገድ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በዚህም የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!