የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአፋር ክልል የዱብቲ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ

By Meseret Awoke

January 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በአፋር ክልል የዱብቲ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ፡፡

በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የጤናማ እናትነት ወር አስመልክቶ በአፋር ክልል የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዱብቲ ሆስፒታል በመገኘት የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት የህክምና ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በሆስፒታሉ እየተሰጡ ያሉ የእናቶችና የህጻናት የጤና አገልግሎቶችን የተመለከቱ ሲሆን ፥ በሆስፒታሉ አገልግሎት እየተሰጣቸው የሚገኙ እናቶች በሆስፒታሉ አገልግሎት መደሰታቸውን ለዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

እናቶች በጤና ተቋም ውስጥ እንዲወልዱ በጤና ባለሙያዎች የሚደረገው ክትትልና ድጋፍ አበረታች መሆኑን ተናግረው በሆስፒታሉ የወሊድ አገልግሎት እየተሰጣቸው ለሚገኙ እናቶች የተለያዩ ድጋፎችን ማበርከታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!