በለገጣፎ ለገዳዲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለውጡንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በመደገፍ በለገጣፎ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።
በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ በመደመር የብልፅግና ጉዧችንን እናሳካለን፣ ሃገር በሃሳብና በስራ ይገነባል፣ ከብልፅግና ጋር መጭው ጊዜ ብሩህ ነው የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።
ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች መካሄዳቸው ይታወሳል።
በአዳማ፣ በጅማ፣ በምዕራብ ሃረርጌ እና በሶማሌ ክልል ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፎች መካሄዳቸው የሚታወስ ነው።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision