የየካቲት 11 ቀን 45ኛ ዓመት በመቐለ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመቐለ ከተማ ትግራይ ስታዲየም ተከበረ።
ማለዳ ላይ በዓሉን በማስመልከት በሰማዕታት ሀውልት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ነባር ታጋዮች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
እለቱ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት በትግራይ ስታዲየም ተከብሯል።
በአከባበሩ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነባር ታጋዮች ተገኝተዋል።
በዓሉ ላለፈው አንድ ወር በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር ቆይቶ ዛሬ የማጠቃለያ ክብረ በዓል ነው የተከናወነው።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision