ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና ምንም ዓይነት ቴክኖሎጂ ከውጪ ሳታስገባ የሰራችው አውሮፕላን በዚህ ዓመት ለሽያጭ ይቀርባል

By Alemayehu Geremew

January 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ምንም ዓይነት የግንባታ ቁስ እና ቴክኖሎጂ ከውጪ ሳታስገባ የሰራችውን ሲ 919 የተሰኘ የመንገደኞች አውሮፕላን በዚህ ዓመት ለሽያጭ እንደምታቀርብ አስታውቀች፡፡

መቀመጫውን በሻንጋይ ያደረገው የቻይና የንግድ አይሮፕላን ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ዉ ዮንግሊያንግ ÷ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሲ 919 ፕሮጀክት ላይ ያደረሰውን ጉዳት መቆጣጠር መቻሉን እና የአውሮፕላን ግንባታ ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካው ቦይንግ አምራች ኩባንያ እና ፈረንሣይ የሚገኘው ኤርባስ በትሪሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር በዘርፉ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበረ ሲጂቲ ኤን አስታውሷል፡፡

ይህም እስከ ፈረንጆቹ 2025 ሀገሪቷ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ሁሉንም ምርቶች ቻይና ውስጥ ለማምረት የነደፈችውን ስትራቴጂ ከወዲሁ ያሳካ ነው ተብሎለታል፡፡

የቻይናው ሲ 919 አውሮፕላን በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 21 ቀን 2020 ከሁቤይ ግዛት ውሃን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመነሳት የሙከራ በረራውንም ማድረጉ ተመላክቷል።