ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያቀረበችው ጥያቄ በቻይና እና ሩሲያ ታገደ

By Meseret Awoke

January 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለተባበሩት መንግስታት ያቀረበችው ጥያቄ በቻይና እና ሩሲያ መታገዱ ተገለጸ፡፡

ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ማስወንጭፏን ተከትሎ በአምስት ሰሜን ኮሪያውያን ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አሜሪካ ያቀረበችው ጥያቄ ነው በቻይና እና በሩሲያ የታገደው፡፡

ቻይና የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ ዝግ ስብሰባ ከማድረጉ በፊት በሀገሪቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ከዋሽንግተን የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ያደረገች ሲሆን፥ ሩሲያም በተመሳሳይ መንግድ የአሜሪካን የማዕቀብ ጥያቄ መቃወሟ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አባል አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ የሁለቱን ሀገራት ውሳኔ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፥ ቻይና እና ሩሲያ ጥያቄያችንን ውድቅ ማድረጋቸው በአሜሪካ ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም ብለዋል፡፡

ማዕቀቡ ኢላማ የተደረገው ከቻይና ጋር ግንኙነት ባላቸው የሰሜን ኮሪያ ድርጅቶች ተወካዮች ላይ መሆኑን ቲ አር ቲ ወርልድ በዘገባው አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!