የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮችና አባላት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

January 22, 2022

አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን #ወደሀገርቤት ጥሪን ተቀብለው የመጡትን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ማህበራት ተወካዮች እና አባላትን ተቀብለው ማነጋራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮችን እና አባላትን አግኝተው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገርቤት ጥሪን ተከትለው ወደ ሀገር ቤት መምጣታቸው ይታወቃል፡፡