የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዓመታዊ የባህላዊ ስፖርቶች ውድድር ተጀመረ

By Feven Bishaw

January 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዓመታዊ የልዩ ልዩ ባህላዊ ስፖርቶች ውድድር በአሶሳ ከተማ ተጀመረ፡፡

በውድድሩ ትግል፣ በ12 እና 18 ጉድጓድ ገበጣ፣ ኩርቦ፣ ቡብ እና ሻህ የተሰኙ ባህላዊ ስፖርቶች እንደሚያካትት የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ትዕዛዙ ታዬ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ ገልጸዋል፡፡