ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያ መንግስት የፓርላማ አባላት ምርጫ እንዲቀጥል ወሰነ

By Alemayehu Geremew

January 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ መንግስት የተጓተተውን የሀገሪቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ እንዲቀጥል በመወሰን የምርጫ መርሀ ግብሩን ይፋ አደረገ፡፡

የምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት ከተጀመረ በኋላ ተቋርጦ የነበረበት የ ጋልሙዱግ ክልል÷ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ 21 የፓርላማ አባላትን እንደሚመርጥም ተወስኗል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ሁሴን ሮብሌ ሰብሳቢነት ሚመራው የሀገሪቷ የምክክር ምክር ቤት በጥር ወር መጀመሪያ ባካሄደው ስብሰባ ÷ ሁሉም አስመራጭ ኮሚቴዎች የህዝብ ምክር ቤት አባላት ምርጫውን እንዲያፋጥኑ አሳስቧል።

እያንዳንዱ ፌዴራላዊ ክልልም ምርጫ የሚያካሂድበትን ቀነ ገደብ ከወዲሁ እንዲያሳውቅ ምክር ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የሀገሪቱ የፓርላማ ምርጫ የካቲት 25 እንዲካሄድም ስምምነት ላይ መደረሱን ነው ዘ ኢስት አፍሪካን የዘገበው፡፡