የሀገር ውስጥ ዜና

የጣና ሐይቅን ከእምቦጭ አረም ስጋት የሚታደግ ሰፊ ሕዝባዊ ንቅናቄ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል

By Feven Bishaw

January 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣና ሐይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ ከ120 ሺህ በላይ ሕዝብ የሚሳትፍበት ንቅናቄ በሚቀጥለው ሳምንት በማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንደሚጀመር የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የእምቦጭ አረም ማስወገድ ዘመቻ የ2013 ዓ.ም አፈፃጸምና የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ በጎንደር ከተማ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል፡፡