ቴክ

የሰውነት ሙቀትን የሚለይ ሮቦት ተሰራ

By Tibebu Kebede

February 19, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ተመራማሪዎች ያልተለመደና ወጣ ያለ የሰውነት ሙቀትን የሚለይ ሮቦት ሰርተዋል።

አዲሱ ሮቦት ሰው በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ከተለመደው ወጣ ያለ የሰውነት ሙቀት ያለባቸውን ሰዎች መለየት የሚችልና ማንነታቸውን የሚያነብ ነው ተብሏል።

ሮቦቱ በአንድ ጊዜ ከአንድ ሰው በላይ ሙቀትን መለየትና መለካት የሚችል ሲሆን፥ የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንደሚረዳም ነው የተነገረው።

አውሮፕላን ማረፊያዎ፣ ሆስፒታሎችና ሌሎች ሰው የሚበዛባቸውና የሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሮቦቱ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተመራማሪዎቹ ያለሰው እገዛ ለተላላፊ በሽታ መጠጊያ የሆኑ ነገሮችን በጨረር በመታገዝ የሚያፀዳ ሌላ ሮቦትም ሰርተዋል።

ሁለቱም ሮቦቶች ታዲያ በውሃን ከተማ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታትና የተጠቂዎችን ቁጥር ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ናቸው።

ምንጭ፦ ሺንዋ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision