Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልልና የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል እና የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ህገ ወጥ ንግድ፣ የሰዎች እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጄኔራል ነስረዲን አብዲ ተፈራርመውታል።

በስምምነቱ የእርሻ መሬትና የንብረት ስርቆት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በባህል ፌስቲቫል፣ በንግድ ትርዒትና ባዛር እንዲሁም በኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ለማጠናከር እንደሚሰሩም ተገልጿል።

የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ልዑክ በአማራ ክልል ለሶስት ቀናት ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።

በቆይታውም የወረታ ደረቅ ወደብ ምረቃን ጨምሮ፣ በባርዳር ከተማ ልዩ ልዩ የልማት ተቋማትንና በጣና ኃይቅ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች መጎብኘቱን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.