የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከክሊንተን ሄልዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆይ ፉማፊ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

January 26, 2022

አዲስ አበባ፣ጥር 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከክሊንተን ሄልዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የቦርድ አባል ጆይ ፉማፊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታን ጨምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ጥራትን ማሻሻል እና ያለውን አጋርነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

በተጨማሪም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ፣ በጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋም ጥረቶች እና በአጠቃላይ የጤና ስርዓት ግንባታን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!