ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን የዱባይ በረራ የፊታችን ቅዳሜ እንደሚጀምር አስታወቀ

By Mekoya Hailemariam

January 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጦት የነበረውን የዱባይ በረራ የፊታችን ቅዳሜ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ቀጥታ ወደ አገሯ የሚደረጉ በረራዎችን ከልክላ መቆየቷ ይታወቃል።

ሀገሪቱ ይህንን ክልከላ ማንሳቷን ተከትሎ ነው ዓየር መንገዱ በረራውን የሚጀምረው።