83ኛው የሰማዕታት ቀን ተከበረ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 83ኛው የሰማዕታት ቀን ተከበረ ።
በ6 ኪሎ ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት አደባባይ በነበረው አከባበር ላይ በዕለቱ ለተሰው ሰማዕታት የህሊና ፀሎት ተደርጓል።
በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ አቶ እንዳወቅ አብጤ፣ አባት አርበኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የፖሊስ ማርች ባንድ ዕለቱን የሚዘክሩ ሙዚቃዎችን አቅርበዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተወከሉ ተማሪዎችም ስነ ስርዓቱን በዝማሬ አጅበዋል።
ልለቱን የሚዘክሩ የተለያዩ ትዕይንቶች የቀረቡ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሮ በ6 ኪሎ የሰማዕታት ሃውልት አደባባይ የነበረው መርሀ ግብር ተጠናቋል።
ዕለቱ በ1929 ዓ.ም በወቅቱ የኢትዮጵያ አገረ ገዢ በነበረው ሮዶልፎ ግራዚያኒ በግፍ የተጨፈጨፉ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚታወሱበት ነው።
በርስቴ ፀጋዬ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision