Fana: At a Speed of Life!

1ኛው የፌደራል እና የክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነሮች የጋራ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የፌደራል እና የክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ የምክክር ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው “የሀገሪቱ ማረሚያ ቤቶች ሰብዓዊ መብት እና የህግ የበላይነት የሚከበርባቸው ውጤታማ የማረምና ማነጽ ማዕከላት እናደርጋለን!” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሁሉም ክልል ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

በጉባኤው በፀጥታ፣ በታራሚዎች አያያዝ እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.