ጠፍቶ የነበረው የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ዘውድ ተመለሰ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኔዘርላንድስ መንግስት ጠፍቶ የነበረውን የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ዘውድ አስረከበ።
ዘውዱን የኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ በዛሬው እለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስረክበዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ዘውዱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተረክበዋል።
ዘውዱ ከ1985 ዓ.ም. አንስቶ ጠፍቶ የቆየ ሲሆን፥ በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም. በኔዘርላንዷ ሮተርዳም ከተማ ተገኝቷል።
የኔዘርላንድስ መንግሥትም ይህን ቅርስ ለኢትዮጵያ መመለስ ጠቃሚ መሆኑን በማመን፥ ዘውዱን ለመመለስ ሁኔታዎች ሲያመቻች መቆየቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘውዱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ላመቻቹት ለሲራክ አስፋውና ለኔዘርላንድስ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision