ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ፍትህ ቀንን አስመልክቶ ኢዜማ ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ፍትህ ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
የውይይት መድረኩ “ማህበራዊ ፍትህ መረጋጋት እና የጋራ እድገት ለተረጋገጠ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።
በውይይት መድረኩ ላይ የማህበራዊ ፍትህ ፍልስፍና መሠረት በሚል ርዕስ መነሻ ፅሁፍ ቀርቧል።
የአካል ጉዳተኞች፣ የሴቶች፣ ህፃናት እና ሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ማህበራዊ ፍትህን አስመልክቶ በኢትየጵያ ያለው አተገባበር ምን ይመስላል? የሚሉ የመወያያ ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
በትዝታ ደሳለኝ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision