የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

By Tibebu Kebede

February 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር አብርሃም በላይ እና የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ ተገኝተዋል።